Psalm 51

July 10, 2026

መዝሙር 51(1-9)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤
እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤
እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።

በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።
አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፥
እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።
እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፤ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።

በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤
እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።
ሐሤትንና ደስታን አሰማኝ፥
የሰበርሃቸውም አጥንቶቼ ደስ ይላቸዋል።
ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ፥
በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።